SAʴý

የተባበሩት መንግሥታት ዓርማ፥ ኒውዮርክ የተባበሩት መንግሥታት ዓርማ፥ ኒውዮርክ  (©Lewis Tse Pui Lung - stock.adobe.com)

ብጹዕ ካርዲናል ፓሮሊን በ79ኛው የተባበሩት መንግሥታት ጉባኤ ላይ እንደሚገኙ ተገለጸ

የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብጹዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊል በኒውዮርክ በሚካሄደው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እንደሚገኙ ታውቋል። ብጹዕነታቸው በ @TerzaLoggia በተሰኘ ማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ እንደገለጹት፥ በኒውዮርክ ከመስከረም 12-20/2017 ዓ. ም. በሚካሄደው የ2024 ከፍተኛ የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ተገኝተው ቅድስት መንበር የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አባል የሆነችበት 60ኛ ዓመት በመስዋዕት ቅዳሴ ጸሎት እንደሚያከብሩ ታውቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብጹዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን በአሜሪካ ኒውዮርክ ከተማ ተገኝተው ከመስከረም 12-20/2017 ዓ. ም. በሚካሄደው 79ኛ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከፍተኛ ጉባኤን ላይ እንደሚሳተፋ ታውቋል።

79ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ፥ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቻርተር ላይ የተመሠረተ የባለ ብዙ ወገን መፍትሄዎችን በማስተዋወቅ እና የ2030 አጀንዳ እና የዘላቂ ልማት ግቦችን ተግባራዊ ለማድረግ የተደረጉ ጥረቶችን በማፋጠን ላይ እንደሚያተኩር ታውቋል። ከጉባኤው ቀዳሚ ርዕሠ ጉዳዮች መካከል ዓለም አቀፍ ሰላምን እና ደህንነት መደገፍ፣ ዘላቂ ልማትን ማስተዋወቅ፣ የአየር ንብረት ለውጥን መዋጋት፣ የብዝሃ ሕይወት መጥፋት እና የአካባቢ ብክለት የሚሉ ይገኙበታል።

 

21 September 2024, 16:06