SAʴý

በኢትዮጵያ የሶዶ ሀገረ ስብከት አዲስ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ደጀኔ ሂዶቶ በኢትዮጵያ የሶዶ ሀገረ ስብከት አዲስ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ደጀኔ ሂዶቶ   (courtesy of Pax Catholic TV, Ethiopa)

በሶዶ ካቶሊካዊ ሀገረ ስብከት የአዲስ ጳጳስ ሹመት በታላቅ መንፈሳዊ ሥነ-ሥርዓት ተፈጸመ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በደቡብ ኢትዮጵያ ለሶዶ ሀገረ ስብከት አዲስ ጳጳስ መሾማቸውን ተከትሎ የብጹዕ አቡነ ደጀኔ ሂዶቶ ሹመት መስከረም 5/2017 ዓ. ም. በታላቅ ሥነ-ሥርዓት ተፈጽሟል። ተሿሚው ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ደጀኔ ሂዶቶ በወላይታ ሶዶ ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በተከናወነው ታላቅ መንፈሳዊ ሥነ-ሥርዓት ላይ ቃለ መሐላቸውን በመፈጸም የሶዶ ሀገረ ስብከት አዲስ ጳጳስ ሆነው ተሹመዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ተሿሚው ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ደጀኔ ሂዶቶ መስከረም 5/2017 ዓ. ም. በሶዶ ሀገረ ስብከት ቅድስት ሥላሴ ካቶሊካዊ ካቴድራል በተከናወነው ታላቅ መንፈሳዊ ሥነ-ሥርዓት ላይ ቃለ መሐላቸውን በመፈጸም ከሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ካርዲናል አቡነ ብርሃነየሱስ እጅ የጵጵስና ማዕረግ ተቀብለዋል።

ሐዋርያዊ ሹመት የተሰጣቸው ብጹዕ አቡነ ደጀኔ ሂዶቶ ከበዓሉ ሥነ-ሥርዓቱ ቀደም ብለው በሀዋሳ ከተማ አቅራቢያ በሚገኝ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የጸሎት እና የሱባኤ ማዕከል መንፈሳዊ ዝግጅት ካደረጉ በኋላ ወደ ሶዶ ሲደርሱ በከተማው ከንቲባ፣ በአካባቢው የመንግሥት ባለስልጣናት፣ በብጹዓን ጳጳሳት፣ ካኅናት፣ ደናግል፣ ምዕመናን እና ጥሪ በተደረገላቸው እንግዶች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ተሿሚው ጳጳስ አቡነ ደጀኔ ወደ ሶዶ ሲደርሱ የተደረገላቸው አቀባበል
ተሿሚው ጳጳስ አቡነ ደጀኔ ወደ ሶዶ ሲደርሱ የተደረገላቸው አቀባበል

በበዓሉ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ተገኝተዋል
እሑድ መስከረም 5/2017 ዓ. ም. የቀረበውን መስዋዕተ ቅዳሴ የመሩት የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝዳንት ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነየሱስ ሲሆኑ በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ከቀድሞው የሶዶ ካቶሊክ ሀገረ ስብከት ጳጳስ የነበሩት ብጹዕ አቡነ ጸጋዬ ቀነኒ እና የአዲግራት ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ተስፋሥላሴ በስተቀር ሁሉም ጳጳሳት ተገኝተዋል። በበዓሉ ላይ ከ250 በላይ ካህናት፣ የልዩ ልዩ አብያተ ክርስቲያናት፣ የሙስሊም ምዕመናን ተወካዮች እና በሺዎች የሚቆጠሩ ምእመናን ተካፋይ ሆነዋል።

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት በኢትዮጵያ የቅድስት መንበር እንደራሴ ጽሕፈት ቤት ጸሐፊ ሞንሲኞር ማሲሞ ካተሪን ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የተላከውን መልዕክት በንባብ በማሰማት የአባ ደጀኔን የሶዶ ሀገረ ስብከት መሪነት መደበኛ የጵጵጽና ሹመት ሕጋዊነት አረጋግጠዋል።

ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነየሱስ በመስዋዕተ ቅዳሴው ሥነ-ሥርዓት ላይ ባሰሙት ስብከት፥ የአዲሱን ጳጳስ ሹመት በደስታ ተቀብለው፥ ከሀገረ ስብከቱ ምዕመናን ጋር በመሆን ሁሉም ሰው አቡነ ደጀኔን በጸሎት እና በቅን አገልግሎት እንዲደግፏቸው አሳስበዋል። ብጹዕነታቸው ለአቡነ ደጀኔ ባስተላለፉት መልዕክትም፥ ቤተ ክርስቲያኒቱን በታማኝነት በሙሉ ልብ እንዲያገለግሏት፣ ዘወትር ለመንጋው መልካም እረኛ እንዲሆኑ፣ ድሆችን እንዲወዱ እና ምዕመናኑን እንዲያዳምጧቸው አደራ ብለዋል።

በሕመም ምክንያት በሥነ-ሥርዓቱ ላይ መገኘት ያልቻሉት የቀድሞው የሶዶ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ጸጋዬ እና ሀገረ ስብከቱን በጊዜያዊ ሲመሩ የቆዩት ብጹዕ አቡነ ስዩም ፍራንሷ የአጋርነት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። የመንግሥት ባለስልጣናት፣ በኢትዮጵያ የካፑቺን ፍራንችስኮስውያን ወንድሞች ገዳም አለቃ እና የሀገረ ስብከቱ የምእመናን ተወካዮችም ድጋፋቸውን ለአቡነ ደጀኔ ገልጸዋል።

አባ ደጀኔ ከሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነየሱስ እጅ የጵጵስና ማዕረግ ሲቀበሉ
አባ ደጀኔ ከሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነየሱስ እጅ የጵጵስና ማዕረግ ሲቀበሉ

የተባበረ የጸሎት እና ድጋፍ ጥያቄ
ብጹዕ አቡነ ደጀኔ በሥነ-ሥርዓቱ ማጠቃለያ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፥ ሐዋርያዊ አገልግሎታቸው “የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ” (ዮሐ. 2፡5) በሚለው የቅድስት ድንግል ማርያም ትዕዛዝ እንደሚመራ ገልጸው፥ በሉርድ የቅድስት ድንግል ማርያም መገለጥ፥ ቤተ ክርስቲያንን ያለማቋረጥ እንዲያገለግሉ የሚያስታውሳቸው መሆኑንም ተናግረዋል። ከዚህም በተጨማሪ በተለይ በኢትዮጵያ የሚከናወኑ የአምልኮ ሥርዓቶችን በተመለከተ በላቲን የአምልኮ ሥርዓት ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት ቤተ ክርስቲያኒቱን ለማገልገል ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል።

ብጹዕ አቡነ ደጀኔ በንግግራቸው ማጠቃለያ፥ በስመተ ጵጵስና በዓላቸው ላይ ለተገኙት ብጹዓን ጳጳሳት፣ ለካኅናት፣ ለገዳማውያን እና ገዳማውያት፣ ለክቡራት እና ክቡራን እንግዶች እንዲሁም ለካቶሊካዊ ምዕመናን በሙሉ ምስጋናቸውን አቅርበው የተባበረ የጸሎት ድፋቸውን&Բ;͠ይቶዋል።

ብጹዕ አቡነ ደጀኔ በመደምደሚያቸው፥ ኃይል እና ብርታት የሆኑት የሀገረ ስብከቱ መላው ምእመናን ወጣቶችንም ጨምሮ በጊዜያዊ ተግዳሮቶች እና ዓለማዊ ጉዳዮች ተስፋን ሳይቆርጡ ከአባቶቻቸው የተቀበሉትን እምነት ጠብቀው በተጨባጭ እንዲኖሩት አደራ ብለዋል።

የሶዶ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ደጀኔ ሂዶቶ
የሶዶ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ደጀኔ ሂዶቶ

 

 

 

23 September 2024, 12:56