SAʴý

የማድራስ-ሚላፖር ሃገረ ስብከት ህፃናት በልዩ ትምህርተ ክርስቲያናዊ መርሃ ግብሩ ላይ በተሳተፉበት ወቅት የማድራስ-ሚላፖር ሃገረ ስብከት ህፃናት በልዩ ትምህርተ ክርስቲያናዊ መርሃ ግብሩ ላይ በተሳተፉበት ወቅት 

የሕንድ ቤተ ክርስቲያን ህፃናትን በሃይማኖት ውስጥ ለማሳተፍ የሚያስችል ልዩ ሥነ ሥርዓቶችን አስተዋወቀች

በህንድ የሚገኘው የማድራስ-ሚላፖር ሃገረ ስብከት የሕፃናት ልጆችን እምነት ለማጠናከር የታለሙ ተከታታይ አዳዲስ ትምህርተ ክርስቲያናዊ መርሃ ግብሮችን ማስተዋወቁ ተነግሯል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

በሃገረ ስብከቱ የሃይማኖት አስተምህሮ ኮሚሽን ቁጥጥር ሥር የሚመሩት እነዚህ ተነሳሽነቶች ህፃናቱ ከጥምቀት ጀምሮ እስከ የመጀመሪያ ቅዱስ ቁርባን ድረስ ባሉ ጊዜያት ያላቸውን መንፈሳዊ እድገት ለማዳበር የተነደፉ ናቸው ተብሏል።

በህንድ የሚገኘው ‘ካቶሊክ ኮኔክት’ የሚባለው የካቶሊክ የዜና አገልግሎት እንደገለጸው የፕሮግራሙ አራት ዋና ዋና አዲስ የተዋወቁት “ቅድመ የቤተክርስቲያን ሚስጥራት” ህፃናቱን በተለያዩ የሃይማኖት ትምህርቶቻቸው ውስጥ በንቃት እንደሚያሳትፉ ተገልጿል።

በእሁድ መስዋእተ ቅዳሴ ወይም በልዩ የበዓል ቀናት የሚካሄዱት እነዚህ ሥነ ሥርዓቶች ህፃናቱ ከእምነታቸው ጋር የበለጠ ግንኙነት እንዲኖራቸው ለማድረግ እና ንቁ የቤተሰብ ተሳትፎን ለማበረታታት ያለመ ነው ታብሏል።

ከዚህም ባለፈ ተነሳሽነቱ መደበኛ ትምህርታቸውን ያልጀመሩ ህፃናት በተለያዩ መዝሙሮች፣ መንፈሳዊ ግጥሞች እና ቀልዶች እምነታቸውን የሚገልጹበት የመስከረም ወር ዝግጅትንም እንደሚያካትት እና ዝግጅቱ አስደሳች እና እንግዳ ተቀባይነት መንፈስን ለመፍጠር በሚል እንደ ቸኮሌት ያሉ ጣፋጭ ምግቦችን እና ታዋቂ ገጸ-ባህሪያትን በማካተት ልምዱን አስደሳች እና ለታዳጊ ህፃናት ተደራሽ ለማድረግ ታስቦ እንደሚዘጋጅም ተገልጿል።

የአንደኛ ክፍል ተማሪዎች “የህይወት ዘመን መስቀል” ተብሎ የሚጠራው እና በአዋቂዎችም ዘንድ ተወዳጅነት ያገኘውን፣ ጠቃሚ የሆኑ መጽሃፍ ቅዱሳዊ ጥቅሶች የተጻፈበት የብረት መስቀል እንደሚሰጣቸው ተብራርቷል።
ይህ በሕጻናት እና በምእመናንም ጭምር የሚደረገው መስቀል በካህናት የተባረከ ሲሆን፥ በሚከፋፈልበት ወቅትም የነገረ መለኮት ማብራሪያ እንደሚሰጥበት ተነግሯል።

ሃገረ ስብከቱ ሦስተኛ ክፍል ላሉ ሕፃናት የጸሎትን አስፈላጊነት የሚያመለክት ከእንጨት የተሰራ መቁጠሪያ እና የቆዳ ቦርሳ የሚያቀርብ ሲሆን፥ በዚህ ሥነ ሥርዓት ወቅት ወላጆች እንደ ቤተሰብ ለመጸለይ በመስማማት ለልጆቻቸው የጸሎት ሕይወት ድጋፋቸውን እንዲሰጡ ይጋበዛሉ።

የአምስተኛ ክፍል ተማሪዎች በየዕለቱ መጽሐፍ ቅዱስን እንዲያነቡ የሚያበረታታ ማስታወሻ በእንግሊዝኛ እና በታሚል ቋንቋ የተዘጋጀ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚሰጣቸው እና ይህ የንባብ ክህሎታቸውን ለማዳበር ተብሎ የሚሰጣቸው ስጦታ የቅዱሳት መጻሕፍት ጥናትን ከዕለት ተዕለት ተግባራቸው ጋር ለማዋሃድ እንዲረዳቸው ታልሞ እንደሚሰጣቸውም ጭምር ተገልጿል።

እነዚህ መርሃ ግብሮች ባለፈው ዓመት ከማህበረሰቡ አስደሳች ግብረ መልስ ያገኙ ሲሆን፥ አጎራባች ሀገረ ስብከቶችም ተመሳሳይ ተግባራትን ለመፈጸም ፍላጎት ማሳየታቸው ተጠቁሟል።

ከዚህም በተጨማሪ እነዚህ መርሃ ግብሮች ወጣት ካቶሊኮችን በማነሳሳት ለመንፈሳዊ እድገታቸው የበኩላቸውን አስተዋፅዖ እንደሚያደርጉ ተስፋ እንዳለው ኮሚሽኑ ገልጿል።
 

18 September 2024, 14:19