SAʴý

የጣሊያን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር በማልታ ፓላዞ ኦርሲኒ ውስጥ በተዘጋጀው "በላውዳቶ ሲ መንፈስ ጉዞ ወደ ኮፕ-29" በሚል ርዕስ በተዘጋጀ ከፍተኛ ደረጃ ጉባኤ ላይ ንግግር ሲያደርጉ የጣሊያን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር በማልታ ፓላዞ ኦርሲኒ ውስጥ በተዘጋጀው "በላውዳቶ ሲ መንፈስ ጉዞ ወደ ኮፕ-29" በሚል ርዕስ በተዘጋጀ ከፍተኛ ደረጃ ጉባኤ ላይ ንግግር ሲያደርጉ 

84 በመቶ የሚሆነው ወጣቱ ትውልድ የአየር ንብረት ቀውስ መጪውን ጊዜ አደጋ ላይ እንደሚጥል ያስባል ተባለ

በአዘርባጃን ከሚካሄደው የኮፕ-29 የአየር ንብረት ቀውስ ጉባኤ ቀደም ብሎ በቅድስት መንበር የማልታ ሉዓላዊ ሰራዊት ማህበር ኤምባሲ የሃይል ሽግግርን አስመልክቶ ባዘጋጀው ከፍተኛ ደረጃ ውይይት ላይ የተሳተፉት ተናጋሪዎች ይህ ሽግግር በዓለም አቀፍ ደረጃ ወጣቶችን እያስጨነቀ ያለውን የአየር ንብረት ለውጥ ተግዳሮቶችን በተጨባጭ ለመቋቋም የሚያስችሉ አዳዲስ ስልቶችን እንዴት ማፍራት እንደሚቻል ለቫቲካን ዜና ገልጸዋል።

 አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

ሮማ ውስጥ በሚገኘው ታዋቂው የፓላዞ ኦርሲኒ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ በተካሄደው ከፍተኛ ደረጃ ውይይት ላይ የተሳተፉት በኒውዮርክ የሚገኘው የፎርድ-ሃም ጋቤሊ የንግድ ትምህርት ቤት አማካሪ የቦርድ አባል እና ሚላን ውስጥ የሚገኘው የቅዱስ ልበ ኢየሱስ የካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር ክርስቲና ፊኖቺ ከስብሰባው ጎን ለጎን ከቫቲካን ዜና ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደገለጹት በቅርብ ጊዜ የዓለም አቀፍ ታዳሽ ኃይል ኤጀንሲ ባደረገው ጥናት ከ10,000 ወጣቶች መካከል 84 በመቶ ያህሉ የአየር ንብረት ቀውሱ የወደፊት ህይወታቸውን አደጋ ላይ የሚጥል ነገር እንደሆነ አድርገው እንደሚቆጥሩ በመግለጽ፥ ወጣቶቹ የመፍተሄው አካል ለመሆን እና ለውጥ ለማምጣት ተግባራዊ መሳሪያዎች እንደሚያስፈልጋቸው አብራርተዋል።

ሰኞ መስከረም 6 ቀን 2017 ዓ.ም. በቅድስት መንበር የማልታ ሉዓላዊ ሰራዊት ማህበር ኤምባሲ ባዘጋጀው ዝግጅት ላይ የቫቲካን ፋውንዴሽን ምሁራንም ጭምር ንግግር እንዳደረጉ ተገልጿል።

ምሁራኑ የኢነርጂ ሽግግር አዲሱን ትውልድ “በእርግጠኝነት ዓለምን ሊያሻሽል በሚችሉ” ለውጦች ውስጥ ለማሳተፍ ቁልፍ መንገድ መሆኑን በአጽንዖት በመግለጽ፥ በኢኮኖሚ ደረጃ ብቻ ሳይሆን “በማህበራዊ አካታችነት” ረገድም ምን ዓይነት ‘ተግባራዊ አካሄድ’ እንደሚያስፈልግም አመላክተዋል።

ዶክተር ክርስቲና ከአዲሱ ትውልድ ጋር ብዙ መስራት የሚያስችሉ መንገዶች እንዳሉ በመጠቆም፥ “ይህ ዘርፍ ወደ ሕይወት ከሚያመጣቸው አዳዲስ ሙያዎች አንፃር የዚህ ሂደት ወሳኝ አካል ሊሆኑ ይችላሉ” ሲሉ የተናገሩ ሲሆን፥ “በመላው ዓለም ዙሪያ ባሉ የአዲሱ ትውልድ መካከል የጋራ ቋንቋ እና ሂደት ጋር የተያያዙ ‘እድሎችን’ ማቅረብ እንደሚያስፈልግም ጭምር ገልጸው፥ ወጣቱ ትውልድ እንደዚህ አይነት ተግባራዊ መሳሪያዎች ያለው በሃይል ሽግግር ላይ ብቻ ሳይሆን በኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ አከባቢዎች ላይም ለውጥ እንደሚያመጣ አሳስበዋል።

“በላውዳቶ ሲ መንፈስ ወደ ኮፕ-29”
“በላውዳቶ ሲ መንፈስ ወደ ኮፕ-29 ጉባኤ፡ የኢነርጂ ሽግግር ለማህበራዊ እና ለስራ ዕድል ፈጠራ” በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ዝግጅት በአዘርባጃን ከህዳር 2 እስከ 11 ቀን 2017 ዓ.ም. በሚካሄደው የኮፕ 29 ጉባኤ ላይ በሚቀርበው በሜይር ፋውንዴሽንን የተጠናውን ጥናት እና ግኝቶች ላይም እንደተወያየ የተነገረ ሲሆን፥ የጣሊያን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ማትዮ ፒያንቴ-ዶሲም ከተናጋሪዎቹ መካከል እንደነበሩ ተገልጿል።

ከዚህን ቀደም በዱባይ በተካሄደው የኮፕ-28 ጉባኤ ላይ የቀረበው ይህ ጥናት ጣሊያን፣ እንግሊዝ፣ አሜሪካ፣ ቱርክ፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ፣ ቻይና፣ ህንድ፣ አልጄሪያ እና ቺሊን ጨምሮ ከአስር ሀገራት የተውጣጡ 1,700 ምላሽ ሰጪዎችን እንዳሳተፈ ተነግሯል።

የሜይር ፋውንዴሽን (MAIRE Foundation) ጥናት የተካሄደው ከዓለም አቀፍ የገበያ ጥናትና አማካሪ ድርጅት (IPSOS) ጋር በመተባበር እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፥ የተሟላ የጥናት ውጤቶቹን በተቋሙ ድረ-ገጽ ላይ ማማከር እንደሚቻል፥ ይህም የሰው ልጆችን ችግር ለማቃለል የሚጥሩ እና ለኃይል እና ዲጂታል ሽግግር አስተዋፅኦ ለማድረግ ሰፊ እይታቸውን እና ሁለገብ እውቀታቸውን ተግባራዊ ማድረግ የሚችሉትን ‘የወደፊቱ ሰብአዊ መሐንዲሶችን' ለመፍጠር ስልጠናዎችን በማስፋፋት ድርጅቱ ያለውን ቁርጠኝነት ያረጋግጣል ተብሏል።

ለትውልድ ቀጣይነት ያለው መጪው ጊዜን ለማቅረብ ተጨባጭነት ያስፈልጋል መባሉ
የዓለም ሙቀት መጨመር እና የአየር ንብረት ለውጥን ለመዋጋት ከቅሪተ አካል ነዳጆች ወደ ታዳሽ እና ተመላላሽ የኃይል ምንጮች መሸጋገር አስፈላጊ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፥ አዳዲስ ክህሎቶች እና አሁን ያለው የሰው ኃይል ብቃት ለዚህ ሽግግር ወሳኝ መሆኑን ተገልጿል።

ጥናቱ በተለይ በእስያ፣ በመካከለኛው ምስራቅ፣ በሰሜን አፍሪካ እና በደቡብ አሜሪካ ባሉ ታዳጊ ሀገራት ያለውን የኃይል ሽግግር ለመቅረፍ የክህሎት እድገት አስፈላጊነት ግንዛቤ እያደገ መምጣቱን እና ከዚህም በላይ በሥነ-ምህዳር ሽግግር ውስጥ ከእነዚህ ክልሎች የሚወጣውን አዲስ የንቃተ ህሊና እና የአመራር ሚና ወሳኝ መሆኑን ያመላክታል።

በጥናቱ እንደተረጋገጠው ይህንን ለውጥ የሚመሩት መሐንዲሶች ሽግግሩን መቋቋም የሚቻልባቸው አካሄዶች ላይ የበለጠ “ሰብአዊነት ያለው” አቀራረብ መከተል እንዳለባቸውም ጭምር ገልጿል።

አባ ፎርቱናቶ 'ትልቁ ጥያቄ ለልጆቻችን ምን ትተን እናልፋለን?’ ማለታቸው
በአሲሲ ‘የፍራንቼስኮ ኢኮኖሚ’ ተብሎ በሚታወቀው ላይ ትልቅ ሚና የተጫወቱት የቅዱስ ጴጥሮስ ቤተ ክርስቲያን ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት አባ ኢንዞ ፎርቱ-ናቶ፣ ዓለም ለቀጣዩ ትውልድ ስላለበት ኃላፊነት እና “የዓለም የወደፊት ዕጣ ፈንታ” በወጣቱ ትውልድ ላይ የተመሰረተ እንደሆነ ለቫቲካን ዜና ገልጸው፥ 'ትልቁ ጥያቄ ለልጆቻችን ምን ትተን እናልፋለን?’ የሚለው ነው ካሉ በኋላ፥ የራሳችንን ኃላፊነት መገንዘብ እንደሚገባም አሳስበዋል።

አባ ፎርቱናቶ በማከልም “የሰው ልጅ የዓለም ባለቤት (‘ዶሚነስ’) አይደለም፥ ይልቁንስ የሰው ልጅ መሆን ያለበት ዓለምን ወደ አንድ አቅጣጫ እንዲሰበሰብ የሚያደርግ ነው ተብሎ ይታሰባል” ብለዋል።

አምባሳደር ዛናርዲ ላንዲ የማልታ ማህበር ማህበረሰቦችን ለሚያሰቃዩ ታላላቅ ችግሮችን ለመቅረፍ ፍላጎት አሳይቷል ማለታቸው
በቅድስት መንበር የማልታ ሉዓላዊ ሰራዊት ማህበር አምባሳደር አንቶኒዮ ዛናርዲ ከግጭቱ በስተጀርባ ያለውን የማህበሩን መነሳሳት አስመልክተው ከቫቲካን ዜና ጋር ቆይታ ያደረጉ ሲሆን፥ ምንም እንኳን እኛ በተለይ በሃይል ሽግግር ላይ 'ባለሙያዎች' ባንሆንም በጉባኤው ለመሳተፍ እና ታዳሚዎች ዛሬ በህብረተሰባችን እና በዓለማችን ውስጥ ባሉ በጣም ሚስጥራዊነት ያላቸው እና አስፈላጊ ጭብጦች ላይ እንዲሳተፉ ለማድረግ ጓጉተናል ብለዋል።

ሁለት ዓለማትን ማገናኘት
አምባሳደር ዛናርዲ በመጨረሻም “በቤተክርስቲያኑ አስተምህሮ መሰረት መልካም ነገር ከሚያደርጉ ትላልቅ የኢጣሊያን ኩባንያዎች ጋር ተባብረን ለመስራት እንጥራለን፥ በዚህም አካሄድ በእነዚህ ሁለት ዓለማት መካከል እንደ መገናኛ ነጥብ ለመሆን እንሞክራለን” ብለዋል።
 

19 September 2024, 15:07