SAʴý

በሀገረ ስብከት ውስጥ ሌላ ካኅንም ተይዘው ታስረዋል በሀገረ ስብከት ውስጥ ሌላ ካኅንም ተይዘው ታስረዋል 

በኒካራጓ የማታጋልፓ ዘርዓ ክኅነት ትምህርት ቤት ዳይሬክተር በጸጥታ ኃይሎች መያዛቸው ተነገረ

የኒካራጓ ባለስልጣናት የማታጋልፓ ዘርዓ ክኅነት ትምህርት ቤት ዳሬክተር የሆኑትን አባ ጃርቪን ቶሬዝን መያዛቸው ታውቋል። የሳንታ ማሪያ ደ ጉዋዳሉፕ ቁምስና መሪም የሆኑት አባ ጃርቪን ቶሬዝ ከረዳታቸው ራዮ ባልማሴዳ ጋር ከሐምሌ 29/2016 ዓ. ም. ጀምሮ መታሰራቸውን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ገልጸዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

የኒካራጓ ባለስልጣናት ሐምሌ 29/2016 ዓ. ም. በማታጋልፓ ሀገረ ስብከት ውስጥ ሌላ ካኅን ይዘው ማሰራቸው ታውቋል። በሳን ሉዊስ ጎንዛጋ ከፍተኛ ዘርዓ ክኅነት የፍልስፍና ትምህርት ቤት ዳይሬክተር አባ ጃርቪን ቶሬዝ ወደ እስር ቤት መወሰዳቸውን የቁምስናው ምዕመናን ለመገናኛ ብዙኃን ገልጸዋል።

በሀገሪቱ የሚገኙ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እና ድርጅቶች የአባ ጃርቪን መታሰር አውግዘው፥ የአባ ጃርቪን ረዳት በሴባኮ ራዮ ባልማሴዳ መታሰሩን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች አስታውቀዋል።

በኒካራጓ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ 13 ካኅናት የታሰሩ ሲሆን፥ አብዛኛዎቹ የማታጋልፓ ሀገረ ስብከት ካኅናት ሲሆኑ፥ ይህ ሀገረ ስብከት ከጥር 5/2016 ዓ. ም. ጀምሮ በግዞት የሚገኙት የአቡነ ሮላንዶ አልቫሬዝ ሀገረ ስብከት እንደ ሆነ ታውቋል።

ቅድስት መንበር ከመጋቢት ወር 2016 ዓ. ም. ጀምሮ ግንኙነቷን ሙሉ በሙሉ ባታቋርጥም ነገር ግን ዲፕሎማሲያዊ ጽሕፈት ቤቶቿን እንድትዘጋ የኒካራጓ መንግሥት መጠየቁ ይታወሳል።


 

07 August 2024, 15:59